ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

Tuesday, 23 July 2019 09:14

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት ለ2012 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ በማታ እና በሣምንት መጨረሻ መርሐግብር መስፈርቱን የሚያሟለ አዲስ አመልካቶችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡

Read more: ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

 

የ2011 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2012 ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

Saturday, 10 August 2019 18:05

የዩኒቨርሲቲው የ2011 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2012 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ በዩኒቨርሲቲው ካውንስል ሐምሌ 24 እና 25/2011 ዓ/ም ተገምግሟል፡፡ ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

Read more: የ2011 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2012 ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

ቤኔፊት ሪያላይዝ ፕሮጀክት በ4 ወረዳዎች በሚገኙ የሙከራ ጣቢያዎች የመስክ ምልከታ አካሂዷል

Wednesday, 07 August 2019 15:50

ቤኔፊት ሪያላይዝ ፕሮጀክት በተለያዩ 4 ወረዳዎች በሚገኙ የሙከራ ጣቢያዎች ከሐምሌ 15-19/2011 ዓ/ም የመስክ ምልከታ አካሂዷል፡፡ በምዕራብ አባያ ወረዳ በያይቄና በዛላ ጉትሻ ቀበሌዎች የአደንጓሬ፣ የበቆሎና ድንች እንዲሁም በደራሼ ወረዳ በሆልቴ፣ በቁጫ ወረዳ በጋሌ፣ በዛላ ወረዳ በሜላ ባይሳ ቀበሌዎች በተመሳሳይ የበቆሎና የማሽላ  የሙከራ ሥራዎች ምልከታ ተደርጎባቸዋል፡፡ ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

Read more: ቤኔፊት ሪያላይዝ ፕሮጀክት በ4 ወረዳዎች በሚገኙ የሙከራ ጣቢያዎች የመስክ ምልከታ አካሂዷል

 

የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በ‹‹አረንጓዴ አሻራ ቀን›› ከ19 ሺ በላይ ችግኞችን ተከለ

Friday, 02 August 2019 17:35

የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ሐምሌ 22 በተደረገው ‹‹የአረንጓዴ አሻራ ቀን›› በቤሬ ተራራና በዩኒቨርሲቲው ሁሉም ካምፓሶች ከ19 ሺ በላይ ችግኞችን በመትከል አሻራውን አኑሯል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከተከላው ባሻገር 75 ከመቶ በላይ ችግኞችን ለከተማው በማቅረብና በወዜ ተራራ ላይ ከ13 ሺ በላይ የችግኝ መትከያ ጉድጓዶችን በማዘጋጀት የድርሻውን አበርክቷል፡፡ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

Read more: የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በ‹‹አረንጓዴ አሻራ ቀን›› ከ19 ሺ በላይ ችግኞችን ተከለ

ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራና የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ሥልጠና ተሰጠ

Friday, 02 August 2019 17:39

ለዩኒቨርሲቲው ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና የፒ ኤች ዲ ተማሪዎች ‹‹Multi-Physics Modeling and Simulation Opportunities and Challenges›› በሚል ርዕስ እንግሊዝ አገር በሚገኘው ማንችስተር ዩኒቨርሲቲ የውኃ ዘርፍ መምህርና ተመራማሪ በሆኑት የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ምሩቅ ዶ/ር ሮቤል ጥላዬ አማካይነት ከሐምሌ 11-13/2011 ዓ/ም የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ ሥልጠናው በዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ምሩቃን ማኅበር፣ በውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትና በሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በውኃ ግድቦች አስተዳደር፣ በወንዝ ተፋሰስ አስተዳደር፣ በአየር ንብረት ለውጥ ሞዴሎች እንዲሁም በተለያዩ የምልከታ መሣሪያዎች ዙሪያ ያተኮረ ነው፡፡ ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

Read more: ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራና የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ሥልጠና ተሰጠ

 

More Articles...

Page 1 of 222

«StartPrev12345678910NextEnd»