- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የተዘጋጀውና የእንሰት እርሾን ለረዥም ጊዜ በቤተ-ሙከራ ለማስቀመጥና ለአርሶ አደሮች አባዝቶ ለማከፋፈል ያለመው ፕሮጀክት ከዓለም ዓቀፉ የዘረመል ምኅንድስና እና ባዮቴክኖሎጂ ማዕከል የ45 ሺህ ዩሮ ድጋፍ አግኝቷል፡፡
Read more: የእንሰት እርሾን ለረዥም ጊዜ በቤተ-ሙከራ ለማስቀመጥና ለአርሶ አደሮች አባዝቶ ለማከፋፈል የተቀረፀው ፕሮጀክት የ45 ሺህ ዩሮ ድጋፍ አገኘ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ትምህርት ቤት ከተማሪዎች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ላላቸው የሥነ-ልቦና፣ ጋይዳንስና ካውንስሊግ እና የዜሮ ፕላን ባለሙያዎች፣ የተማሪዎች አገልግሎት ሠራተኞች እንዲሁም የተማሪዎች መኝታ ቤት፣ የምግብ አገልግሎት፣ የሰላም ፎረምና የደኅንነትና ጥበቃ አስተባባሪዎች የአዕምሮ ጤና፣ ሥነ ልቦናና ማኅበራዊ አገልግሎት አሰጣጥንን በተመለከተ ከኅዳር 10-11/2013 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: ሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህርይ ሳይንስ ትምህርት ቤት የአዕምሮ ጤና፣ ሥነ-ልቦናና ማኅበራዊ አገልግሎትን በተመለከተ ሥልጠና ሰጠ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ‹‹ኢኖቬቲቭ እንሰት ሪሰርች ፕሮጀክት›› የእንሰት ምርት ሂደትን የሚያግዙ ማሽኖችን በቴክኖሎጂና በፈጠራ በመሥራት የዩኒቨርሲቲው፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አመራራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት ኅዳር 29/2013 ዓ/ም ለማኅበረሰቡ አስተዋውቋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለ2012 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ፣ ለሕክምና (Medicine) 4ኛ እና 5ኛ ዓመት እንዲሁም ለሕግ 4ኛ ዓመት ተማሪዎች ከኅዳር 24 - 27/2013 ዓ/ም የምዝገባ ጊዜ እንዲሁም ኅዳር 28/2013 ዓ/ም መደበኛ ትምህርት የሚጀመርበት ሲሆን በ2012 ዓ/ም ተመራቂ ያልነበሩ ተማሪዎች የመግቢያና የምዝገባ ጊዜም ወደፊት በማስታወቂያ በሚገለፀው መሠረት የሚከናወን መሆኑን ያስታውቃል።
- Details
The university seeks competent, committed and interested Ethiopian academic staff to assign for the EXECUTIVE DIRECTOR POSITION for SGS.
Here is the full details for the Vacancy.