በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የባዮሎጂ ትምህርት ክፍል በ‹‹Infectious Diseases›› 3ኛ ዲግሪ እንዲሁም በ ‹‹Bio-Medical Sciences›› 2ኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራም ለመክፈት የሚያስችለውን የውጭ ሥርዓተ-ትምህርት ግምገማ ነሐሴ 26/2012 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የቤኒፊት ሪያላይዝ ፕሮግራም ክልላዊ የአማካሪ ምክር ቤት ጉባዔ በመስክ ጉብኝትና የ2020 የ6 ወራት ሪፖርት ግምገማ በማድረግ ከነሐሴ 26 - 27/2012 ዓ/ም ለሁለት ቀናት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የሐዋሳና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሮጀክት አፈፃፀም ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት ለ2013 የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በሣምንት መጨረሻ መርሐ ግብር መስፈርቱን የሚያሟለ አዲስ አመልካቶችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡

icon ሙሉ መረጃውን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ

In this pandemic era, AMU hosting 33rd Virtual Convocation at New hall, Main Campus on 5th September, 2020, saw 2,326 graduating of which 1,823 are males and 506 females. This batch has 1,233 Master and 1,093 Undergraduates from all streams being taught in the university via Regular, Distance & Continuing modes of education.

Dignitaries like Gamo Zone Administrator, Mr Birhanu Zewede, Jinka University President, Prof Gebre Entiso, other invited guests and AMU community graced the event which was live on Facebook and YouTube from 8.30 am onwards for the home viewers. Click here to see the pictures

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር በመደበኛ፣ በክረምት፣ በሳምንት መጨረሻ እና በተከታታይና ርቀት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 2,326 ተማሪዎች ቅዳሜ ነሐሴ 30/2012 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል፡፡ የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱም በዩኒቨርሲቲው ፌስቡክ ገጽ እና ዩቲዩብ ቻናል በቀጥታ ተላልፏል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ