የዩኒቨርሲቲው “RUNRES” ፕሮጀክት ከመጀመሪያ ዙር ቆይታው የ2 ዓመታት አፈፃፀሙን ለመቃኘት ኅዳር 02/2014 ዓ/ም በኃይሌ ሪዞርት ወርክሾፕ አዘጋጅቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ከአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች በኢንተርንሺፕ ላይ የቆያችሁ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መመለሻ ጊዜ ኅዳር 24/2014 ዓ.ም ሲሆን የመመዝገቢያ ጊዜ ከኅዳር 24-26/2014 ዓ.ም መሆኑን እያሳወቀ ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመለሱ በኢንተርንሺፕ ላያ የቆያችሁበትን ሪፖርት አጠናቅቃችሁ ለሚመለከተው ፋከልቲ ገቢ እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው በጥብቅ ያሳስባል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሁሉ አቀፍ ሴክተር ዳይሬክቶሬት ከአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለባለድርሻ አካላት፣ ለቢሮ ኃላፊዎችና ከ19ኙ ቀበሌያት ለተወጣጡ 70 በጎ መልዕክተኞች ከኅዳር 2-4/2014 ዓ/ም በአስተሳሰብ ለውጥና በማኅበራዊ ጉዳይ ተግባራት ላይ የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ፈጠራ ልማት ማፍለቂያ ማዕከል ከኢትዮጵያ ሥራ ፈጠራ ልማት ማዕከል ጋር በመተባበር በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መምህራን ከጥቅምት 29 -ኅዳር 4/2014 ዓ/ም የሥራ ፈጠራ ክሂሎት የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ፎቶፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህሪ ሳይንስ ት/ቤት ‹‹የትምህርት ምዘናና ግምገማ ሚና ለትምህርት ጥራት›› በሚል ርዕስ ለትምህርት አመራር አካላት ኅዳር 1/2014 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ