በጫሞ ሐይቅ ዙሪያ ለሚሠራው አሳታፊ ዘላቂ የመሬትና የውሃ አያያዝ ሥራ ዕቅድ አዘገጃጀት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ከ10 ወረዳዎች ለተወጣጡ 58 የልማት ጣቢያ ሠራተኞችና የዘርፉ ባለሙያዎች ከሐምሌ 13/2012 ዓ/ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዓባያ ካምፓስ ለ7 ቀናት ተሰጥቷል፡፡ ሥልጠናው በጀርመን ልማት ተራድኦ ድርጅት/GIZ/ እና በግብርና ሚኒስቴር የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮጀክት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ያዘጋጁት ነው፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በ1ኛ ዓመት የክረምት መርሃ-ግብር ለመመዝገብ አመልክታችሁ የስም ዝርዝራችሁ በማስታወቂያ ሠሌዳ የተገለፀ ተማሪዎች የትምህርት ክፍያና የምዝገባ ጊዜ ከነገ 29/11/2013 - 1/12/2013 ዓ.ም በመሆኑ በተከታታይና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በመቅረብ የማስታወቂያ ሠሌዳው ላይ የተለጠፈውን የትምህርት ክፍያ ዝርዝር በማየት ክፍያ እየፈፀማችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይና ርቀት ት/ኮሌጅ

የእንግሊዝ ኤምባሲ የ UK መንግሥት የ “Chevening Scholarship Award” አሰጣጥን በተመለከተ በ28/11/2013 ዓ/ም የመጀመሪያ ዲግሪ ላላቸው የአ/ም/ዩ መምህራንና ሠራተኞች በበይነ-መረብ ማብራሪያ ይሰጣል ፡፡

በመሆኑም የመጀመሪያ ዲግሪና ሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ያላችሁ ሠራተኞች ለመወዳደር የሚያስችለውን ግንዛቤ ለማግኘት ከላይ በተጠቀሰው ዕለት ከቀኑ 8፡00 - 9፡30 ድረስ የሚካሄደውን ውይይት ከታች በቀረበው አድራሻ በመጠቀም መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

‹‹ኢትዮጵያን እናልብሳት›› በሚል መሪ ቃል በ3ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ቤሬ ተራራ ላይ በሚገኘው ተፋሰስና በሁሉም የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች ሐምሌ 20 እና 23/2013 ዓ/ም የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሂዷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ