የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ት/ቤት ማኅበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለአርባ ምንጭ ከተማ ማኅበራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች በተለያዩ የሕግ ጉዳዮች ዙሪያ ከግንቦት 18-19/2013 ዓ.ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ማኅበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከምዕራብ ዓባያና ከአርባ ምንጭ ከተማ ለተወጣጡ የ1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን ግንቦት 14/2013 ዓ/ም የተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ንባብ ክሂሎት ማሻሻያ ዙሪያ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ በሥልጠናው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፊደላት፣ ድምጽና ስያሜያቸው እንዲሁም ተነባቢና አናባቢ ድምጾች በቃላት ውስጥ ሲገቡ የሚያመጡትን ለውጥ ለተማሪዎቹ የሚያስተምሩበት ስነ-ዘዴ በስፋት ተዳሷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የባህልና ቋንቋ ጥናት ኢንስቲትዩት ከኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 5ኛው ‹‹ሀገረሰባዊ ዕውቀት ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገት›› ሀገራዊ ዓውደ ጥናት ግንቦት 26/2013 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ተካሂዷል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሁሉ አቀፍ ሴክተር ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲው ማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ማኅበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ባዘጋጁት መድረክ በጫሞ ካምፓስ አካባቢ ካሉ ነጋዴዎች ጋር በወጣት ተማሪዎች ስብዕና ግንባታና የነጋዴው ማኅበረሰብ ባለው ሚና ዙሪያ ግንቦት25/2013 ዓ/ም ውይይት ተካሂዷል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Arba Minch University in association with Ministry of Culture & Tourism has hosted 5th national meet on ‘Indigenous Knowledge for National Development’ on 3rd June, 2021, at Main Campus. State Minister for Culture and Tourism, Mrs Bizunesh Meseret, many regional, zonal officials and stakeholders graced the event. Click here to see the pictures