በግብርና ሣይንስ ኮሌጅ የዕፅዋት ሣይንስ ተመራቂ ተማሪዎች የመመረቂያ የተግባር ምርምር ሥራዎቻቸውን ግንቦት 26/2009 ዓ.ም በግብርና ሣይንስ ኮሌጅ የዕፅዋት ምርምር ማዕከል አቅርበዋል፡፡ በተመራቂ ተማሪዎቹ ከቀረቡ ሥራዎች መካከል የበቆሎ፣ ሸንኮራ አገዳ፣ ቦሎቄ፣ ጥቅል ጎመን፣ ካሮትና ስኳር ድንች ላይ የተሠሩ ምርምሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ::

የዕፅዋት ሣይንስ ትምህርት ክፍል 35 የተግባርና 11 የንድፈ ሀሣብ  በድምሩ 46 ኮርሶች እንዳሉት የገለፁት የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ መምህር ኪያ አዳሬ የተግባር ትምህርቱ  ተማሪዎች በንድፈ ሀሣብ የተማሩን ሥራ ላይ በማዋል በሣይንሳዊ ሂደት  ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ ሥራዎችን እንዲያከናውኑ ያስችላል ብለዋል፡፡

የኮሌጁ የምርምር አስተባባሪ ዶ/ር ራህማቶ ነጋሽ በበኩላቸው ትምህርት ክፍሉ ተወዳዳሪ ምሁራንን ለማፍራት በተማሪዎችና በመምህራን አበረታች የተግባር ምርምሮችን እያከናወነ መሆኑን  ገልጸዋል፡፡

ተመራቂ ተማሪ ይበሉ ተሰማ በሰጠው አስተያየት የተግባር ትምህርቱ ሣይንሳዊ የግብርና ዘዴን የተከተለ በመሆኑ በንድፈ ሀሣብ የተማሩትን ወደ ተግባር ለመቀየርና በግብርናው መስክ ወደ ሥራ ዓለም ሲገቡ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ መሆኑን ተናግሯል፡፡

የዕፅዋት ሣይንስ ትምህርት ክፍል በ2006 ዓ/ም የተመሠረተ ሲሆን ከሚያስተምራቸው 163 የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች 47ቱ በዘንድሮው ዓመት ይመረቃሉ፡፡ በተጨማሪም በአፈር ሣይንስ፣ የሠብል ልማት፣ የመስኖ ሠብል ልማትና የሸንኮራ አገዳ አመራረትና ቴክኖሎጂ የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች 43 ተማሪዎችን በመደበኛና በሣምንት መጨረሻ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡