ለኮሚዩኒቲ ት/ቤት ተማሪዎች በውጤታማነት ትግበራ አሠራር ሥርዓት ፅንሰ ሃሳብ፣ በትምህርት ቤቱ የ2009 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እና በሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርት  አሰጣጥ ላይ ከጥቅምት 1-2/2010 ዓ/ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠና እየተሠጠ ነው፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ::

በመጀመሪያው ቀን በጧቱ የስልጠና ጊዜ ስለውጤታማነት ትግበራ አሠራር ሥርዓት ግንዛቤ ማስጨበጫ ገለፃ የተደረገ ሲሆን ከሠዓት በኋላ ደግሞ በት/ቤቱ የ2009 ዓ/ም አፈፃፀም ላይ ሪፖርት ቀርቦ  ውይይት ተካሂዷል፡፡ ኩረጃን የሚጠየፍ ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም ዜጋ መረባረብ እንዳለበት ተሰምሮበታል፡፡በሁለተኛው ቀን  በሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርት አሰጣጥ  እና ተፈላጊውን ባህርይ ከመቅረፅ አኳያ መከናወን ስለሚገባቸው ተግባራት ላይ ስልጠናው የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በዚህ ስልጠና ከ7ኛ-8ኛ ክፍል ያሉ 150 ያህል ተማሪዎች እና ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ያሉ 400 ተማሪዎች በድምሩ 550 የሚሆኑ ተማሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት