ለአ/ምንጭ ከተማና አካባቢው ማኅበረሰብ በሙሉ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 3ኛውን “የማኅበረሰብ ሣምንት” “በተፈጠረው ዕድል ማኅበረሰቡን እናገልግል!” በሚል መሪ ቃል በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ በአውደ ርዕይና ፓናል ውይይት ከሰኔ 19-22/2010 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ ያከብራል፡፡    

በአውደ ርዕዩ በዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተማሪዎች ተሰርተው ለአካባቢው ማኅበረሰብ ሊሸጋገሩ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን፣ የምርምር ውጤቶችን መሰረት ያደረጉ ሞዴሎችንና በማኅበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ የተከናወኑ አበይት ተግባራትን የሚያሳዩ ሥራዎች ይቀርባሉ፡፡

በመሆኑም የአርባ ምንጭ ከተማና አካባቢው ማኅበረሰብ በተጠቀሱት ቀናት በዋናው ግቢ የሚካሄደውን አውደ ርዕይ በመጎብኘት ለዩኒቨርሲቲው ቀጣይ የማኅበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ የበኩላችሁን አስተያየት እንድታበረክቱ ዩኒቨርሲቲው ከታላቅ አክብሮት ጋር ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

“በተፈጠረው ዕድል ማኅበረሰቡን እናገልግል!”

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ