ማሳሰቢያ

አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የካቲት 17/2010 ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሠረት ለውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያመለከታችሁ ተወዳዳሪዎችን የማጣራት ሥራ በማጠናቀቅ ለፅሑፍ ፈተና ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በቀድሞው ማስታወቂያ 2.75 የመመረቂያ ነጥብ ለወንዶችና 2.5 የመመረቂያ ነጥብ ለሴቶች ኑሯችሁ ለሌክቸራርነት እንዲሁም 2.5 እና ከዚያ በላይ ኑሯችሁ ለቴክኒካል አሲስታንትነት አመልክታችሁ ለፅሁፍ ፈተና ያልተጋበዛችሁ (Not Selected) የሆናችሁትን እንዳላችሁ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በየዘርፉ የተጠቀሰውን አነስተኛ መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ የፅሁፍ ፈተናውን ሐምሌ 26፣ 2010 ዓ/ም በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በመገኘት እንድትወስዱ ማሻሻያ የተደረገ መሆኑን እንገልፃለን፡፡