ዩኒቨርሲቲው በአዲስ አበባ ዙሪያ በቡራዩ አካባቢ በሚኖሩ ወገኖች ላይ የተፈፀመውን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በጽኑ አውግዞ በዜጎች ላይ በደረሰው ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ከመኖሪያቸው መፈናቀል የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

ዩኒቨርሲቲው የተጎዱ ወገኖቹን መልሶ ለማቋቋም 3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲው መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ወገኖች የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ ተስማምተው በማሰባሰብ ላይ ይገኛሉ፡፡

በንፁኀን ወገኖች ላይ ይህን እኩይ ተግባር የፈፀሙ አካላትና ግለሰቦች በአስቸኳይ ለህግ እንዲቀርቡም ጠይቀዋል፡፡