ማስታወቂያ ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2011 የትምህርት ዘመን የነባር የቅድመና ድህረ-ምረቃ እንዲሁም የተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 1-3/2011 ዓ/ም መሆኑን ያስታውቃል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የአዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዘገባ ጊዜ ወደፊት የሚገለፅ መሆኑን እያሳወቀ በዩኒቨርሲቲው የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ መረጃ በዩነቨርሲቲው ፌስቡክና ድረ-ገፅ  ላይ እንድትከታተሉ  ያሳስባል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከምዝገባው ቀን ቀድመውም ሆነ ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድና ማንኛውንም አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን  በአፅንዖት ይገልፃል፡፡