በአገራዊ የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ ላይ ውይይት ተጀመረ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከመስከረም 28/2011 ዓ/ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ በአገራዊው የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ ዙሪያ የሚደረገው የግብዓት ማሰባሰብያ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የውይይት መድረክ ተጀምሯል፡፡

በመድረኩ በዩኒቨርሲቲው ሥር ባሉ ስድስት ካምፓሶች የሚገኙ ከ 1070 በላይ መምህራንና 600 የአስተዳደር ሰራተኞች ተካፋይ እየሆኑ ይገኛል፡፡

በስድስቱም ካምፓሶች በሚካሄደው የውይይት መድረክ የመጀመሪያ ቀን ውሎ በስድስት የውይይት መነሻ ሰነዶች ላይ ገለፃና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በይዘቱ ዙሪያ የተሰጠውን ስልጠናዊ ውይይት የተካፈሉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ገለፃና ማብራሪያውን አቅርበዋል፡፡

በቀጣይ የውይይት ጊዜያት በሁሉም ካምፓሶች በተዋቀሩ ቡድኖች በቀረቡ ሰነዶች ላይ የቡድን ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡ ከትምህርት ፍኖተ ካርታው በተጓዳኝ የ2010 ዓ/ም እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና እና የ2011 ዓ/ም እቅድ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት