ዩኒቨርሲቲው ከአርባ ምንጭ ከተማና አካባቢው ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በሀገራዊው የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታ ላይ ያተኮረ የግብዓት ማሰባሰቢያ የአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ውይይት መድረክ ጥቅምት 22/2011 / አካሂዷል፡፡ ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

 

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት / ዳምጠው ዳርዛ የውይይት መድረኩን ሲከፍቱ እንደገለጹት ውይይቱ መንግስት በቅርቡ ሀገራዊ የትምህርትና ሥልጠና ሥርዓት ላይ የፖሊሲ ለውጥ ለማድረግና ለማሻሻል ባዘጋጀው የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ላይ ግብዓት የሚሆኑ ምከረ-ሃሳቦችን የመሰብሰብ ሥራ አካል ነው፡፡ ፕሬዝዳንቱ ትምህርት የሀገሪቱ እድገትና ሁለንተናዊ ሥርዓት መገለጫ እንደመሆኑ፣ የሁሉንም ማህበረሰብ ባለቤትነት የሚጠይቅ ጉዳይ ስለሆነ በጉዳዮ ላይ በቂ መረጃ በመለዋወጥ ማህበረሰቡ ለስኬቱ የበኩሉን መወጣት ይገባዋል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ተመሳሳይ መድረኮች እንደ ሀገር ሁሉም ማህበረሰብ የተሳተፈበትና የተግባባበት ወጥ የሆነ የትምህርትና ስልጠና ሥርዓት ለመተግበር፣ እንዲሁም በሚፈለገው ደረጃ ብቁ ዜጎች እንዲፈሩ በማድረግ ሀገራዊ ለውጡን ማገዝ ጉልህ አስተዋጽኦ ያላቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው በዚህ መልኩ ኃላፊነት በመውሰድ በሰነዱ ዙሪያ ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩን ማዘጋጀቱ ይበል የሚያሰኝ በጎ ተግባር መሆኑን ገልፀው ለፍኖተ ካርታው ስኬታማነት በቀጣይ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡም ቃል ገብተዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የትምህርትና ሥልጠና አመራርና አሰራር ሥርዓት ማሻሻያ ሀሳቦችና ችግሮች፣ የከፍተኛ ትምህርት ችግሮች፣ በአጠቃላይ ትምህርትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ምላሽ ተሰቶባችዋል፡፡

በውይይቱ ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር እና በዙሪያው ካሉ 12 ቀበሌያት የተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍል ተሳታፊ ሆነዋል፡፡