የህክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ከዓለም አቀፉ የአልትራሳውን ድፌደሬሽን እንዲሁም ከኢትዮጵያ አልትራሳውንድ ማዕከል ጋር በመተባበር ከአርባምንጭ ሆስፒታልና አካባቢው ለተወጣጡ ሐኪሞች አልትራሳውንድን በአግባቡ መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ከህዳር 3-6/2011 ዓ/ም ሰጥቷል፡፡ ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

በህክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ የህክምና ትምህርት አስተባባሪ ዶ/ር ታዲዮስ ኃይሉ እንደገለፁት የሥልጠናው ዓላማ በህክምናው ዘርፍ ለተሰማሩ ሐኪሞች በአልትራሳውንድ አጠቃቀም ላይ ያላቸውን እውቀትና ክህሎት በማሳደግ መሳሪያውን በተሻለ ሁኔታ እንዲጠቀሙበት ማስቻል ነው፡፡ እንደ ዶ/ር ታዲዮስ ገለፃ ዩኒቨርሲቲው መሰል ሥልጠናዎችን በአካባቢው ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ሲሰጥ መቆየቱን ገልፀው በቀጣይ ምመሰል ሥልጠናዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ህክምና ትምህርት ክፍልየ ውስጥደዌስፔሻሊስት እንዲሁም የጨጓራ፣ አንጀት ናጉበትስፔሻሊስት ሐኪምዶ/ር አብዱልሰመድ መሐመድ እንደገለፁት የአልትራሳውንድ መሳሪያ በቀላሉ የህመምተኛውን በሽታመለየት የሚያስች ልቢሆንም የዘርፉሐኪሞች በሽተኛው የሚሰማውንበተለምዶ ‹‹ምንይሰማሃል?› ›የሚልጥያቄ ከመጠየቅባሻገር መሳሪያውንበአግባቡ ሲጠቀሙበትአይታይም፡፡ ሥልጠናው የባለሙያዎችን በመሳሪያውአጠቃቀም ዙሪያያላቸውን ክህሎት በማሳደግ ለበሽተኞች የተሻለአገልግሎት ለመስጠት ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

ሠልጣኞች በሰጡት አስተያየት ሥልጠናው በአልትራሳውንድ አጠቃቀምላይያላቸውን ክህሎት የተሻለ እንዲሆን ከማስቻሉም በተጨማሪ የህመምተኞችን የጤና ችግር በቀላሉ በመለየትለታካሚዎች የተሻለአገልግሎት እንዲስጥያስችላል ብለዋል፡፡ በቀጣይም ዩኒቨርሲቲው መሰል ሥልጠናዎችን በመስጠት አጋርነቱን ሊያሳይእንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በሥልጠናው ከአርባምንጭዩኒቨርሲቲ፣ ከአርባምንጭ እና ከጊዶሌ ሆስፒታል የተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡