አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከቀድሞ መምህራንና ምሩቃን አሉሙናይ ጋር አራት ኪሎ በሚገኘው የትምህርት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ እሁድ ሕዳር 16/2011 ዓ/ም ከቀኑ 07፡30 ተኩል ጀምሮ ውይይት ያካሂዳል፡፡

በውይይቱ በውጭና በሀገር ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ እያገለገሉ ያሉ የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ መምህራንና ምሩቃን እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች የሚገኙ ሲሆን ውይይቱ በአጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው ሁኔታ እንዲሁም በምርምር፣ በፓርትነርሽፕ፣ በመማር ማስተማርና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች በጋራ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት በማድረግ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ስለሆነም የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ መምህራንና ምሩቃን የሆናችሁ ሁሉ በዚህ መድረክ እንድትታደሙ ዩኒቨርሲቲው በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ