የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግሥት መገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ከዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች ለተወጣጡ 30 የICT ባለሙያዎች በሶፍትዌር ልማት፣ በኔትዎርኪንግ፣ በኮምፒዩተርና ቢሮ ማሽን ጥገና ዙሪያ ከመስከረም 26/2012 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ምስሉን ለማየት ከዚህ ይጫኑ

የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ዶ/ር ቶሌራ ሴዳ እንደገለፁት ሥልጠናው በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያለውን የኮምፒዩተርና ቢሮ ማሽን ጥገና፣ ኔትዎርኪንግና በሶፍትዌር አሠራር ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት ይቻል ዘንድ የባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት ያለመ ነው፡፡

ከደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት መገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ የግል ሥራ ፈጠራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ካሳ ዩኒቨርሲቲውና ኤጀንሲው ባላቸው የሁለትዮሽ ስምምነት መሠረት የተለያዩ የኢንኩቤሽን፣ የምርምር እና የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር ሥራዎችን በጋራ ይሠራሉ ብለዋል፡፡ ለዩኒቨርሲቲው ICT ባለሙያዎች የዕውቀት ሽግግር ለማድረግና ባለሙያዎችን ለማብቃት የጋራ ተልዕኮ ይዘው ሥልጠናውን ማዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል፡፡

ሠልጣኞች በሰጡት አስተያየት ከሥልጠናው አዳዲስ ዕውቀቶችን ማግኘታቸውንና ለወደ ፊቱ ሥራ ፈጣሪ ለመሆን ዕድል የሚከፍት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይ ሥልጠናው ሰፊ ጊዜ ቢሰጠውና ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ICT ባለሙያዎች ቢወስዱት በርካታ ችግሮችን የመፍታት አቅም የሚፈጥር ነውም ብለዋል፡፡