ዩኒቨርሲቲው 6ኛውን ዙር የሕክምና ዶክተሮችን ታኅሣሥ 11/2012 ዓ/ም በዋናው ግቢ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ ያስመርቃል፡፡

በዕለቱ 140 የሕክምና ዶክተሮችን የሚያስመርቅ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 37ቱ ሴቶች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥና የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ይናገር ደሴ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና ተጋባዥ እንግዶች ይገኙበታል፡፡ ምስሉን ለማየት ከዚህ ይጫኑ

ዩኒቨርሲቲው በ2011 ዓ/ም 76 የህክምና ዶክተሮችን ያስመረቀ ሲሆን 19ኙ ሴቶች ነበሩ፡፡

ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት