አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከጋሞ ዞንና ከአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመሆን በደቡብ ክልል 3ኛውን የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማዕከል በዛሬው ዕለት የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አጥናው ካውዛ በተገኙበት በይፋ ሥራ እንዲጀምር አድርጓል፡፡click here to see the the pictures

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግሥት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማዕከሉ በዛሬው ዕለት ወደ ሥራ እንዲገባ በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ማዕከሉ ለጋሞ ዞን ብቻ ሳይሆን በዙሪያው ያሉ ዞኖችንና ልዩ ወረዳዎችን ጭምር የሚያገለግል ነው ብለዋል። ከብዙ ውጣውረድና ልፋት በኋላ የአርባ ምንጭ ምርመራ ማዕከል ዝግጁ እንዲሆን ለተረባረቡ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን በክልሉ ስም አቅርበዋል ።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የቫይረሱ ምርመራ በከተማው እንዲጀመር ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው በቀጣይም አሁን የተቋቋመው የመመርመሪያ ማዕከል ሥረውን ቀጣይነት ባለው ሁኔታ እንዲቀጥል በትኩረት እንሠራለን ብለዋል፡፡ በዚህ ረገድ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብም እንደሚያስፈልግ ፕሬዝደንቱ አክለዋል፡፡

የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺይፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ታምሩ ሽብሩ የምርመራ ማዕከሉ በአንድ ጊዜ 92 ናሙናዎችን መመርመር የሚያስችል ሲሆን ማዕከሉ ሥራ መጀመሩ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገው ከፍተኛ ጥረት ውስጥ ጉልህ ሚና የሚያበረክት ነው ብለዋል፡፡

ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት