በ2012 ዓ/ም ሊሰጥ የነበረው ሀገር አቀፍ የሕግ መውጫ ፈተና (Exit Exam) በኮቪድ-19 መከሰት ምክንያት ወደ 2013 ዓ/ም መተላለፉ ይታወሳል፡፡

ስለሆነም ፈተናው የሚሰጠው ከኅዳር 1-4/2013 ዓ/ም በመሆኑ ፈተናውን መውሰድ የምትፈልጉ በሙሉ ከጥቅምት 2-12/2013 ዓ/ም ድረስ ብቻ ብር 664.00 ( ስድስት መቶ ስልሳ አራት ብር ብቻ) በኤጀንሲው የባንክ ሒሳብ ቁጥር 0171597578400 ገቢ ያደረገባችሁበትን ደረሰኝ በመያዝ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ት/ቤት ቀርባችሁ መመዝገብ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ት/ቤት

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት