በ2012 ዓ/ም በኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደት በ2013 የትምህርት ዘመን እንዲቀጥል መንግሥት በወሰነው መሠረት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎችን ከጥቅም 25 – 26/2013 ዓ/ም የመልሶ ቅበላ መርሃ ግብር ያካሂዳል፡፡

በመሆኑም ተመራቂ ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን በዩኒቨርሲቲው በመገኘት በምትማሩበት ትምህርት ክፍል ሪፖርት እንድታደርጉ እንዲሁም ከጥቅምት 27/2013 ጀምሮ በተመደባቸሁበት መማሪያ ክፍል ተገኝታችሁ ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበትና በትምህርት በምትቆዩበት ወቅት

1. እጆቻችሁን በውሃና ሳሙና በሚገባ መታጠብና የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ዘወትር በሚያስፈልግ ቦታ መጠቀም፣
2. የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ዘወትር በአግባቡ መጠቀም፣
3. አዲስ በተመደባችሁበት የመኝታ ክፍል ብቻ መጠቀም ይኖርባችኋል፡፡

ኮቪድ-19ን በጋራ በመከላከል የመማር ማስተማር ሥራችንን በኃላፊነት እንወጣ!

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት