በኮንሶ ዞንና አካባቢው በተከሰተው የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለሚገኙ ወገኖች ዩኒቨርሲቲው ልዩ ልዩ ኅዳር 15/2013 ዓ/ም ድጋፍ አድርጓል፡፡ በዕለቱ 156 ፍራሽ፣ 28 ካርቶን ሳሙና እና 5 እሽግ የሴቶች የንጽህና መጠበቂያዎች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ከተፈናቃዮቹ በቀረበው ጥያቄ መሠረትም የውሃ አቅርቦት እና የጤና አገልግሎት እየተሰጣቸው ነው፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲው ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የጉማይዴ ከተማ ነዋሪና የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ የማቋቋም ኮምቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ እታለማሁ ንጋቱ ዩኒቨርሲቲው ላበረከተው ድጋፍ በተጎጂ ቤተሰቦችና በወረዳው ስም ምስጋና አቅርበው በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ዩኒቨርሲቲው እና ሌሎችም መንግሥታዊ አካላት ከጎናቸው እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በኮንሶ ዞንና አካባቢው በተከሰተው የእርስ በእርስ ግጭት ከ2,500 በላይ የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በግጭቱ የሰው ሕይወት የጠፋ ሲሆን በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ወ/ሮ እታለማሁ ተናግረዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት