አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው መርሃ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ከ4,500 በላይ ተማሪዎችን ማክሰኞ ጥር 18/2013 ዓ/ም በዓባያ ካምፓስ ሁለገብ ስታዲዬም እንዲሁም ጥር 20/2013 ዓ/ም የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎችን በሳውላ ካምፓስ በደማቅ ሁኔታ ያስመርቃል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት

በዩኒቨርሲቲው ዓባያ ካምፓስ ሁለገብ ስታዲዬም የሚካሄደው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በ EBC ቴሌቪዥን፣ በዩኒቨርሲቲው የፌስቡክ ገጽና የዩቲዩብ ቻናል በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ የዩኒቨርሲቲው አልሙናይ/የቀድሞ ምሩቃን/ ፕሬዝደንት፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ የጋሞ ዞን፣ የአርባ ምንጭ ከተማና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ይገኛሉ፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት