ማስታወቂያ

ለ2012 ዓ/ም 1ኛ ዓመት ለነበራችሁ ተማሪዎች በሙሉ

የሁሉም ካምፓሶች የ2012 ዓ/ም የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ሪፖርት የማድረጊያ ጊዜ ከየካቲት 16-18/2013 ዓ/ም ቀደም ብሎ በማስታወቂያ የተገለጸ ሲሆን ትምህርት የካቲት 22/2013 ዓ/ም የሚጀመር መሆኑን እያሳወቅን ሁሉም የ2012 ዓ/ም የ1ኛ ዓመት የነበራችሁ ተማሪዎች ከሁሉም ካምፓሶች በሕክምናና ፋርማሲ ትምህርት ዘርፍ የተመደባችሁ ሪፖርት የምትታደርጉት በነጭ ሳር ካምፓስ፣ በእንጂነሪንግ የተመደባችሁ በዋናው ካምፓስ፣ ቀደም ሲል በዋናው ካምፓስ ሆናችሁ በእንጂነሪንግ ያልተመደባችሁ በሙሉ በዓባያ ካምፓስ፣ ከሳውላና ጫሞ ካምፓሶች በሕግ የተመደባችሁ በጫሞ ካምፓስ ሆኖ ሌሎቻችሁ በነበራችሁበት ካምፓስ ሪፓርት የምታደርጉ መሆኑን እንገልጻለን።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት