የዩኒቨርሲቲው የምርምር ዳይሬክቶሬት ከቴክኖሎጂና ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች ለተወጣጡ መምህራንና ተመራማሪዎች በምርምር አጻጻፍ ሳይንሳዊ ስነ-ዘዴ ዙሪያ ከየካቲት 9-11/2013 ዓ.ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ የምርምር ንድፈ ሃሳብ አሰባሰብና አጻጻፍ፣ የምርምር ግኝቶች አዘገጃጀትና አጻጻፍ እንዲሁም በታወቁ ጆርናሎች ላይ የሚወጡ ምርምሮች አጻጻፍ ስነ-ዘዴ የሥልጠናው ትኩረቶች ናቸው፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ተሾመ ይርጉ እንደገለጹት የምርምር ተሳትፎ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ይህንን ለመቅረፍ ታልሞ ሥልጠናው ተዘጋጅቷል፡፡ የምርምር ተሳትፎን ማሳደግ የተቋሙንና የተመራማሪውን ደረጃ ከማሳደጉም በተጨማሪ ምርምሮቹ የማኅበረሰቡን ችግር በተግባር ወርደው ሊፈቱ የሚችሉ በመሆናቸው በምርምር አጻጻፍ ዘዴ ላይ ግንዛቤን የሚፈጥር ነው፡፡

የውሃ ሀብት ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሙኤል ዳጋሎ በበኩላቸው ከምርምር ንድፈ ሃሳብ አቀራረብ እስከ ጆርናል ያለውን ሂደት በሥልጠናው በማሳየት ሠልጣኞች ክሂሎታቸውን በማሳደግ ተመራጭ የምርምር ንድፈ ሃሳቦችን እንዲሠሩና ለምርምር ሥራቸው የሚሆን ወጪያቸውን የሚሸፍን ገንዘብ ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር እንዲያፈላልጉነ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

ዶ/ር በሐርቲ ቢሄስቲ እንደገለጹት አብዛኛዎቹ መምህራንና ተመራማሪዎች ጀማሪ በመሆናቸው የምርምር ጽሑፍ አዘገጃጀት በቂ ግንዛቤ የላቸውም፡፡ ሥልጠናው የምርምር ጽሑፍን ለመጻፍ የሚያስችሉ መሠረታዊ ነጥቦችንና ዘዴዎችን በሰፊው በማሳየት በዩኒቨርሲቲው ብቻ ሳይገደቡ ከሀገር ውጪም ምርምሮችን ለመሥራት የሚያስላቸው ክሂሎትና ግንዛቤን ለመፍጠር የሚረዳቸው ነው ብለዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት