የአንደኛውን የእድገትና ትራስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የሁለተኛውን የእድገትና ትራስፎርሜሽን ረቂቅ ዕቅድ እንዲሁም ሌሎች ሀገራዊና ተቋማዊ አጀንዳዎችን ያካተተ ስልጠና ከመስከረም 7/2008 . ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች እየተሰሠጠ ይገኛል፡፡ የስልጠናዉ ተሳትፎ በፎቶ የኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ኮሮፖሬሽን ዘገባ

የስልጠናው ዓላማ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የአምስት ዓመት የእድገትና ትራስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸምና በቀጣዩ ረቂቅ ዕቅድ ላይ በጋራ በመወያየት በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ፣ በልማት ሂደቱ እኩል ተሳታፊ እንዲሆኑ አንዲሁም ፍትሃዊ የጋራ ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ በቀጣይም ለዕቅዱ ተፈጻሚነት ቁርጠኝነታቸውን እንዲያረጋግጡ ማድረግ እንደሆነ ከስልጠናው የተዘጋጀው ሰነድ ያስረዳል፡፡

በተጨማሪም በበቂ ግንዛቤ ላይ የተመሰረቱ ገንቢ ሀሳቦችን እና አስተያየቶችን በማቅረብ የረቂቅ ዕቅዱን ይዘትና ጥራት እንዲያሻሽሉ እና እንዲያዳብሩ የምሁራኑ ብሎም የአጠቃላይ ህበረተሰቡ ሚና ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ከመድረክ ተነስቷል፡፡

የስልጠናው መድረክ በጠቅላይ ሚስትር /ቤት የመሠረተ ልማት ፖሊሲና ዕቅድ አፈጻጻምና ክትትል ሚኒስቴር ዲኤታና የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አባል አቶ ወንድሙ ገዛኃኝ በኢፌዴሪ የፖሊሲ ጉዳዮች የጠቅላይ ሚስትሩ አማካሪ ሚኒስቴር ዲኤታ እና የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታገሠ ጨፎ እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት / ፈለቀ ወልደየስ እየመሩ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ መምህራን፣ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች እና የአስተዳደር ሠራተኞች በአጠቃላይ በዋናው ግቢና በአባያ ካምፓስ የመሰብሰቢያ አዳራሾች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

የመምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች ሥልጠና ሲጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲው ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎች በተያዘላቸው ፕሮግራም መሠረት ከመስከረም 21 እስከ 30/2008 . ባለው ጊዜ ስልጠናው እንደሚሰጣቸው የፕሮግራሙ ዋና አስተባባሪዎች ገልጸዋል ሲል ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳሬክቶሬት ጠቁሟል፡፡