በ2008 ዓ/ም ዩኒቨርሲቲው ለተቀላቀሉ 5700 አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥቅምት 28/2008 ዓ/ም የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም ተካሂዷል ፡፡ Click here to see the Pictures.
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ በመክፈቻ ንግግራቸው ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ዩኒቨርሲቲያችንን ምርጫ አድርጋችሁ የተቀላቀላችሁን ዉድ ተማሪዎቻችን እንኳን በደህና መጣችሁ ብለዋል፡፡በዩኒቨርሲቲው  የመማር ማስተማርና የምርምር ሥራዎች እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎቶች ተማሪዎች ቀጥተኛ ተሳታፊዎች በመሆንና  ለትምህርታቸው ልዩ ትኩረት በመስጠት  ለውጤት እንዲበቁ አሳስበዋል ፡፡ፕሬዝደንቱ አክለዉም ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲዉ የሚኖራቸዉ  ቆይታ መልካም እንዲሆንላቸዉ ተመኝተዋል ፡፡
የዩኒቨርሲቲው የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍስሃ በቀለ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው  የሚኖራቸው ቆያታ የተሳካ እንዲሆን ዩኒቨርሲቲው የሚሰጣቸዉን አገልግሎቶች ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በጥራት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
ተማሪዎቹ  በሰጡት አስተያየት ዝግጅቱ ስለዩኒቨርሲቲዉ አገልግሎት አሰጣጥና ሌሎች ተያያዝ ጉዳዮች እንዲረዱ ያገዛቸዉ ከመሆኑ በተጨማሪ የእንግድነት ስሜት እንዳይፈጠርባቸዉ የረዳቸዉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡አያይዘዉም  እንዲህ አይነት ደማቅ  የእንኳን ደህና መጣችሁ ዝግጅት መደረጉ ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎች ያለዉ ክብር የሚያሳይና በቀጣይ በዩኒቨርሲቲው  ለሚኖራችው ቆይታ ብሩህ ተስፋ  የሚፈነጥቅ ነው ብለዋል ፡፡
በዕለቱ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ሙዚቃና ዉዝዋዜዎች በማቅረብ ለፕሮግራሙ  ድምቀት ሰጥቷል  ፡፡
ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት