የዩኒቨርሲቲው የካፒታልና የመደበኛ በጀት አፈፃፀም እየተሻሻለ መምጣቱን የፋይናንስና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አማረ ጋማ ገልጸዋል፡፡
ከ2007 በፊት በነበረው አፈፃፀም በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር በጀት ተመላሽ ይደረግ  የነበረ ሲሆን ከ2005 – 2007 የበጀት ዓመታት የነበረው አፈፃፀም በንፅፅር ሲታይ  በ2007 የበጀት ዓመት የመደበኛ በጀት አፈፃፀም 98 በመቶ ሲሆን የካፒታል በጀት ደግሞ 92 በመቶ ነበር፡፡በመሆኑም በበጀት ዓመቱ  ከመደበኛ እና ካፒታል በጀት በድምሩ 10 በመቶ ወይም 37 ሚሊየን ብር ብቻ ፈሰስ ተደርጓል፡፡
በ2008 የበጀት ዓመት ለዩኒቨርሲቲው የተመደበው የካፒታልና መደበኛ በጀት 1.2 ቢሊየን ሲሆን ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት አቶ አማረ ሁሉም የሥራ ክፍሎች በፋይናንስ ደንብና መመሪያ መሠረት በጀታቸውን 100%  መጠቀም ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ በተለይም የግዥ ፍላጎቶች በበጀት መዝጊያ ወቅት ተደራርበው በመቅረባቸው ምክንያት ሳይፈፀሙ እንዳይቀሩ የየሥራ ክፍል ኃላፊዎች ክትትል በማድረግ ዕቅዶቻቸውን በወቅቱ አንዲያስፈፅሙ አሳስበዋል፡፡
ዳይሬክቶሬቱ 46 የበጀትና ፋይናንስ ባለሙያዎችን በማቀፍ በመደበኛና ከመደበኛ የሥራ ሠዓት ውጭ ዘወትር ምሽት እስከ ሁለት ሠዓት እንዲሁም በሳምንት መጨረሻ ቀናት ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡