ዩኒቨርሲቲው በ2008 ዓ/ም በቅድመ-ምረቃና በድህረ-ምረቃ የትምህርት ዘርፎች 5,784 አዲስ ተማሪዎችን ከመስከረም 24-25/2008 ዓ/ም ተቀብሎ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ባሉት አንድ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትና አምስት ኮሌጆች በ49 የቅድመ-ምረቃና በ40 የድህረ-ምረቃ የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ መሆኑን በዩኒቨርሲቲው የሬጅስተራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር በለጠ ይልማ ገልፀዋል፡፡ 909 ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ ፣599 በማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ፣1061 በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ፣ 411 በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ 400 በግብርና ሳይንስ ኮሌጅ እና 2353 ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መመደባቸውን የተናገሩት ዳይሬክተሩ ከእነዚህ መካከልም 41 ከመቶው ሴቶች ናቸው ብለዋል፡፡
የተማሪዎችን የመረጃ ልውውጥ በተለይም ምዝገባንና የውጤት መግለጫዎችን በSMIS ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በማድረግ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጥ ጥረት እየተደረገ ሲሆን ምቹ የመማሪያ አካባቢን ለመፍጠር የሚያስችሉ በርካታ የማስፋፊያ ግንባታዎች እየተከናወኑ ነው፡፡
ዩኒቨርሲቲው ባሳለፍነው የ2007 የትምህርት ዘመን በቅድመ-ምረቃና በድህረ-ምረቃ በመደበኛው መርሃ ግብር ከ16 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ያሰለጠነ ሲሆን 4,400 ተማሪዎችን ማስመረቁ የሚታወስ ነው፡፡