የ2008 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የቅድመ-ምረቃ ምሽት ፕሮግራም ሰኔ 16/2008 ዓ.ም በዋናው ግቢ ስታዲየም በልዩ ድምቀት ተከናውኗል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

 

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠዉ ዳርዛ በፕሮግራሙ መክፈቻ ለተመራቂዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት በዩኒቨርሲቲው የነበራቸውን ቆይታ በስኬት አጠናቀው ለዚህ ቀን በመብቃታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው  ይህ ስኬት የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ ባለመሆኑ ወደ ፊት ለበለጠ ኃላፊነት እንዲዘጋጁ አሳስበዋል፡፡

የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝደንትና የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪ ዮርዳኖስ መኩሪያዉ በበኩሉ ‹‹ሳይማር ያስተማረንን ቤተሰብና ማህበረሰብ እንዲሁም ሀገራችንን በሙያችን በቁርጠኝነት ለማገልገል ከፍተኛ ኃላፊነት አለብን›› ብሏል፡፡

የእግር ኳስ ግጥሚያ፣ ገመድ ጉተታ እና የ‹ቅላፄ ባንድ› ዘመናዊና ባህላዊ ሙዚቃዎች ፕሮግራሙን አድምቀዉታል፡፡ በዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና ተመራቂ ተማሪዎች መካከል የተደረገዉ የእግር ኳስ ግጥሚያ ሁለት እኩል በሆነ አቻ ዉጤት የተጠናቀቀ ሲሆን የተመልካችን ቀልብ የሳበዉ የተመራቂ ሴት ተማሪዎችና የአስተዳደር ሴት ሰራተኞች የገመድ ጉተታ ዉድድርም በአቻ ዉጤት ተፈጽሟል፡፡

በፕሮግራሙ የ2008 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች፣ የኮሌጅ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች፣ መ/ራን፣ አስ/ሰራተኞችና ዝግጅቱን ለመታደም የመጡ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ ለበአሉ ድምቀት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡