ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ በክረምትና በርቀት የትምህርት ፕሮግራሞች መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን በአርባምንጭና በሳውላ ካምፓስ ተቀብሎ በመጀመርያ ዲግሪ ከ2011 ዓ.ም ከሐምሌ ወር ጀምሮ ማሰልጠን ይፈልጋል::

Read more: ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

 

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት ለ2011 የትምህርት ዘመን በክረምት መርሐ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል:: 

Read more: ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ONLINE እና በE-LEARNING የታገዘ ትምህርት ለመስጠት ምዝገባ ጀመረ

ዩኒቨርሲቲው ONLINE እና በE-LEARNING የታገዘ ትምህርት ለመስጠት ከ Lucy Consulting Engineers PLC (LUCY) ጋር የመግባቢያ ስምምነት በተፈራረመው መሠረት ትምህርቱን ለማስጀመር ምዝገባ መጀመሩ ተገለፀ፡፡ በፕሮግራሙ አጀማመርና አጠቃላይ ሁኔታ ዙሪያ ከኮሌጅ፣ ትምህርት ቤትና ፋካልቲ ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር  ግንቦት 6/2011 ዓ/ም ውይይት ተካሂዷል፡፡ ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ONLINE እና በE-LEARNING የታገዘ ትምህርት ለመስጠት ምዝገባ ጀመረ

 

የኤች አይ ቪ/ኤድስና ሥነ-ተዋልዶ ጤና ሜይንስትሪሚንግ ሥልጠና ተሰጠ

የሁሉ አቀፍ ሴክተር ዳይሬክቶሬት ከሁሉም ካምፓሶች ለተወጣጡ ተማሪዎች ከሚያዝያ 11-13/2011 ዓ.ም የኤች አይ ቪ እና ሥነ-ተዋልዶ ጤና ሜይንስትሪሚንግ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

የሁሉ አቀፍ ሴክተር ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ መርክነህ መኩሪያ እንደገለፁት የኤች አይ ቪ/ኤድስ ጉዳይ የሰው ልጆች ሁሉ ችግር በመሆኑ ተማሪዎች ባሉባቸው ክበባት ሁሉ የኤች አይ ቪ ጉዳይን እንደ ዋና ተግባር አድርገው እንዲሠሩ ለማድረግ ሥልጠናው ተዘጋጅቷል፡፡ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

Read more: የኤች አይ ቪ/ኤድስና ሥነ-ተዋልዶ ጤና ሜይንስትሪሚንግ ሥልጠና ተሰጠ

ግብርና ሣይንስ ኮሌጅ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ዓውደ ጥናት አካሄደ

ግብርና ሣይንስ ኮሌጅ የእንስሳት ተዋጽኦዎችን (livestock production) በዘመናዊ መልኩ ለማጎልበት እንዲቻል ምርምሮችን እያካሄደ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ኮሌጁ በእንስሳት ምርምር ዙሪያ ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የመጡ የዘርፉ ከፍተኛ ተመራማሪዎች ለዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች ልምዳቸውን በማካፈል የእውቀት ሽግግርን ለመፍጠር በማለም ግንቦት 03/2011 ዓ.ም ዓለም አቀፍ አውደ-ጥናት አካሂዷል፡፡ምስሉን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

Read more: ግብርና ሣይንስ ኮሌጅ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ዓውደ ጥናት አካሄደ