በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሒሳብ ት/ክፍል በ‹‹Numerical Analysis›› ትምህርት ፕሮግራም የ3 ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ወንድማገኘሁ ስምዖን የካቲት 26/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የ3 ዲግሪ ማጠናቀቂያ የምርምር ሥራውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዓባያ ካምፓስ አዲሱ የአስተዳደር ሕንፃ ላይ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ያቀርባል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከል ከዩኒቨርሲቲው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ት/ክፍል እና ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በጫሞ ካምፓስ ለሚገኙ 2ና 3 ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ‹‹Social-Emotional Learning Program›› በሚል ርእስ ከየካቲት 17/2016 ዓ/ም ጀምሮ የ120 ሰዓታት ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

Arba Minch University has rolled out its 9th batch of 70 Doctors of Medicine in a glittering graduation ceremony held in Main Campus on 24th February, 2024. The university has also graduated 3 PhD graduates, 237 masters and 509 undergraduates in different fields of study along with the medical doctors. Of the undergraduates, 33 were Mekelle University students who moved to AMU due to the northern conflict and completed their study since their first year. Click here to see more photos.

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 53 ወንድ እና 17 ሴት በአጠቃላይ 70 የሕክምና ዶክተሮችን ለ9 ጊዜ የካቲት 16/2016 ዓ/ም አስመርቋል፡፡ በመርሃ ግብሩ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይመረቁ የቆዩ ሦስት የ3 ዲግሪ፣ 237 የ2 ዲግሪ እና 509 የመጀመሪያ ዲግሪ በድምሩ 749 ተማሪዎችም ተመርቀዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል 33ቱ ዩኒቨርሲቲው ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ በአደራ ተቀብሎ ያስተማራቸው ናቸው፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

‹‹የዘመኑ ከተሞች ለኢትዮጵያ ብልጽግና›› በሚል መሪ ቃል በወላይታ ሶዶ ከተማ ከየካቲት 09-15/2016 ዓ/ም በተዘጋጀው 9ው የከተሞች ፎረም አርባ ምንጭ ከተማን በመደገፍ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተሳታፊ ሆኗል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡