Print

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ የሥራ ባልደረባ የነበሩት ኢንጂነር ፍቃዱ ፈጠነ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከቀድሞ አርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከአሁኑ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሀይድሮሊክ ምኅንድስና ሐምሌ 5/1995 ዓ/ም እና የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሀይድሮሊክና ፓወር ኢንጂነርንግ ኅዳር 10/2001 ዓ/ም አግኝተዋል፡፡

ኢንጅነር ፍቃዱ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በረዳት ምሩቅ 11፣ በረዳት ሌክቸረርነትና በሌክቸረርነት፣ በአርባ ምንጭ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ዲንነት እንዲሁም በኢንስቲትዩቱ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡ 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በኢንጂነር ፍቃዱ ፈጠነ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይማኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት