ከመስከረም 5 - ጥቅምት 5 የነበረው የ2ኛው ዙር ብሩህ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር የማመልከቻ ጊዜ እስከ ጥቅምት 20/2014 ዓ/ም የተራዘመ ስለሆነ በውድድሩ ለመሳተፍ የጊዜ እጥረት ያጋጠማችሁ ተሳታፊዎች ለውድድሩ ተብሎ በተዘጋጀው ድረ-ገጽ www.bruh.et.com ወይም የኢንተርኔት ችግር ለሚገጥማቸው በዚህ ልጥፍ ውስጥ የተካተተውን የማመልከቻ ቅጽ በመሙላት በፖ.ሳ.ቁጥር 25534 አዲስ አበባ እንድትልኩ እንገልጻለን፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0973078111 ወይም 0911106490 መደወል ይቻላል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ


   የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

 

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ አመራር ዝግጅት ምልመላና ስምሪት ሥርዓት ማስተባበሪያ መመሪያ መሠረት ዶ/ር ሙሉነህ ለማ ወ/ሰማያት የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው የ34 ዓመታት ታሪክ የመጀመሪያውን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በግብርና ሳይንስ ኮሌጅ የእንስሳት ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ ለሆኑት ለዶ/ር ይስሃቅ ከቸሮ ከበደ ሰጥቷል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን በድኅረ ምረቃ 7 እና በቅድመ ምረቃ 674 በአጠቃላይ 681 ተማሪዎች መስከረም 30/2014 ዓ/ም አስመርቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 252ቱ ሴቶች ናቸው፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ      

በዩኒቨርሲቲው 6ኛው ዙር ዓመታዊ የማኅበረሰብ ሳምንት ‹‹በተፈጠረው እድል ማኅበረሰባችንን እናገልግል›› በሚል መሪ ቃል መስከረም 28/2014 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡