Print

ረ/ፕ ማንያዘዋል ከበደ ከአባታቸው ከአቶ ከበደ ወ/መድኅን እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙነሽ ረታ በቀድሞው ጋሞ ጎፋ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ሰኔ 12/1972 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአ/ምንጭ 1 ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአ/ምንጭ አጠቃላይ 2 ደረጃ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡ ሰኔ 26/1991 ዓ/ም ከሀዋሳ መ/ት/ኮሌጅ በፊዚክስ ዲፕሎማ፣ ጥቅምት 10/1998 ዓ/ም ከደቡብ ዩኒቨርሲቲ ዲላ/መ/ት/ጤ/ሳ/ኮሌጅ በፊዚክስ ማስተማር የመጀመሪያ ዲግሪ እና ሐምሌ/2003 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፊዚክስ ትምህርት 2 ዲግሪ ያገኙ ሲሆን ከመስከረም 26/2012 ዓ/ም ጀምሮ የ3 ዲግሪ ትምህርታቸውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል ላይ ነበሩ፡፡

ረ/ፕ ማንያዘዋል ከሐምሌ 01/1991 - መስከረም/1999 ዓ/ም በቀድሞው ጋሞ ጎፋ ዞን ም/ዓባያ ወረዳ ም/ዓባያ 2 ደረጃ ት/ቤት በፊዚክስ መምህርነት፣ ከጥቅምት/1999 – ጥር 2000 ዓ/ም በአ/ም/መ/ት/ኮሌጅ በረዳት ምሩቅ II ያገለገሉ ሲሆን የካቲት 12/2000 ዓ/ም አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን ተቀላቅለው እስከ የካቲት 11/2001 ዓ/ም በረዳት ምሩቅ II፣ ከየካቲት 12/2001 - ሐምሌ 13/2003 በረዳት ሌክቸረር፣ ከሐምሌ 14/2003 - ሐምሌ 25/2011 ዓ/ም በሌክቸረር እና ከሐምሌ 26/2011 ዓ/ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በረ/ፕሮፌሰር አካዳሚክ ማዕረግ ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ረ/ፕ ማንያዘዋል ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ታኅሣሥ 02/2016 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ረ/ፕ ማንያዘዋል የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበሩ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በረ/ፕ ማንያዘዋል ከበደ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት