Print

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ከጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ ጋር በመተባበር በጋሞ ዞን በሚገኙ የተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሳይንስ ቤተ ሙከራዎች ውስጥ ያሉ ኬሚካሎችንና ቁሳቁሶችን የመለየት፣ አስተማማኝ የሳይንስ ቤተ ሙከራዎችን አያያዝ መተግበርና መልሶ የማደራጀት ሥራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር መጋቢት 16/2016 ዓ/ም አካሂዷል፡፡

የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ቴዎድሮስ ብርሃኑ እንደገለጹት የሳይንስ ቤተ ሙከራዎች ውስጥ ያሉ ኬሚካሎችንና ቁሳቁሶችን የመለየት፣ መልሶ የማደራጀትና አስተማማኝ የማድረግ ሥራ በተገቢው ሁኔታ እየተከናወነ ባለመሆኑ ኬሚካሎችን ከመግዛት እስከ ማከማቸትና ማስወገድ ያሉ ተግባራትን ከቤተ ሙከራ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ለመሥራት የሚያስችል ሥልጠና ከጋሞ ዞን ጋር በመስጠት ግንዛቤ ለመፍጠር ታቅዶ እየተሠራ ነው፡፡

በፕሮግራሙ የኮሌጁ የኬሚካል ምኅንድስና መምህርና ተመራማሪ ፍሬው ደነቀ ‹‹Sorting, Identifying, Safe Handling and Re-function Science Laboratory Chemicals and Materials›› በሚል ርዕስ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት