Print

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ አዘጋጅነት ከጥር 25/2016 ዓ/ም ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ የዋናው ግቢ ተማሪዎች የእርስ በእርስ እግር ኳስ ውድድር እየተካሄደ ነው፡፡ ውድድሩ በሁለት ምድብ በስድስት ቡድኖች መካከል የሚከናወን ሲሆን በ2016 ዓ/ም ለሚካሄደው የካምፓሶች ውድድር ዋናውን ግቢ የሚወክሉ ተጫዋቾችን ለመለየት ያለመ ነው፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በተጨማሪም ተማሪዎች የእርስ በእርስ መስተጋብር እንዲያጠናክሩ፣ በትምህርት የደከመ አእምሯቸውን በስፖርት ዘና እንዲያደርጉ እንዲሁም ጤናማ፣ በአካል ብቃት የዳበረ፣ ንቁና የተሻለ አመለካከት ያለው ዜጋ ለመቅረጽ እንደሚረዳ ተገልጿል፡፡

የተማሪዎች ስፖርታዊ ውድድር ሲጠናቀቅ የሠራተኞች የእርስ በእርስ ስፖርታዊ ውድድር በስድስቱም ካምፓሶች የሚቀጥል ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/

ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university

ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/

ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት