በዩኒቨርሲቲው የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በBiology ትምህርት ክፍል የ3ኛ ዲግሪ ዕጩ ተመራቂ ሙላቱ ኦሴ በʻbiodiversity Conservation and Management የትምህርት ፕሮግራም ሲከታተል የቆየውን ትምህርት በማጠናቀቅ ለምርቃት ዝግጁ የሚያደርገውን በʻHabitat Fragmentation Effects on Vascular Epiphytes, Bryophytes and Predator-Pest Dynamics in Kafa Biosphere Reserve and Nearby Coffee Agro-ecosystem, South West Ethiopia በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን የመመረቂያ ጽሑፍ ከውጪና ከሀገር ውስጥ እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው የተጋበዙ ምሁራን በተገኙበት ሰኔ 4/2013 ዓ/ም በዓባያ ካምፓስ ያቀርባል፡፡

የዕጩ ተመራቂው የመመረቂያ ጽሐፍ ሥራ በዩኒቨርሲቲው ማለፍ ያለበትን ደረጃዎች ሁሉ በማለፍ ለዚህ ደረጃ በቅቷል ያሉት የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ፈቃዱ ማሴቦ ዕጩ ተመራቂ ሙላቱ በኮሌጁ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ማጠናቀቁ ምረቃውን ታሪካዊና ልዩ የደርገዋል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ፈቃዱ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ፕሮግራሞች በ3ኛ ዲግሪ ማስመረቅ መጀመሩ ዩኒቨርሲቲው ወደ ፊት እያደገ ስለመምጣቱ ማሳያ መሆኑን ገልፀወ በዚሁ አጋጣሚ ለሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡