የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል የዩኒቨርሲቲያችንን ማኅበረሰብ የሀገራችን ብሔራዊ ጉዳዮችን በሚያገኙት ሚዲያ ሁሉ (በዋነኛነት በሶሻል ሚዲያ ላይ) እንዲያስተጋቡና እንዲያስተዋውቁ ማስተባበር ዋና ተግባሩ ነው፡፡ ለዚህም ተግባር ይረዳ ዘንድ የሀገራችንን ብሔራዊ አጀንዳዎች ለዜጎች በስፋት ማስተዋወቅና ግንዛቤ ማስጨበጥ በጣም አስፈላጊና ቀዳሚ ሥራ ነው፡፡

ስለሆነም ዜጎች የሀገራቸውን ብሔራዊ አጀንዳዎች በሚገባ ተረድተው የሀገራቸውን ጉዳይ በሶሻል ሚዲያም ሆነ በሚያገኙት አጋጣሚ ሁሉ እንዲያስተጋቡና እንዲያስተዋውቁ በሀገራችን ብሔራዊ አጀንደዎች ላይ ያተኮሩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሕዝብ ገለፃ (Public Lecture) እንድታደርጉ ማዕከሉ መድረኮችን ያመቻቻል፡፡ የግቢያችን ምሁራን፣ ተመራማሪዎችና ተማሪዎች ለዜጎች ዕውቀት የሚያስጨብጡ በሀገራችን ብሔራዊ አጀንደዎች ላይ ያተኮሩ የሕዝብ ገለፃ (Public Lecture) እንድታቀርቡ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ በሕዝባዊ ገለጻ መድረኮች ላይ የምታቀርቡትን ርዕስ እና አጽርዖት(summary) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ላይ እንድትልኩልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩነቨርሲቲ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል