በጥናትና ምርምር ተደግፎ ለኢትዮጵያውያን ሕጻናት፣ መምህራንና ወላጆች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ንባብ ክሂል ለመማሪያና ለማስተማሪያ የሚሆን “Easy Ways to Read in English” ወይም “የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፍኖተ-ንባብ” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ታኅሣሥ 26/2014 ዓ/ም ከጧቱ 02፡30 ጀምሮ የዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋና ሥነ-ጽሑፍ ት/ክፍል መምህራን፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ የጋሞ ዞንና በዞኑ የሚገኙ ወረዳዎች የትምህርት ሴክተር ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ መግቢያ በር አካባቢ በሚገኘው አዳራሽ የውይይትና የመጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ይካሄዳል፡፡

ስለሆነም እርስዎም በመርሃ-ግብሩ ላይ በመገኘት የሕጻናትን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ንባብ ችሎታ እንዴት እናሻሽል? ምን ከማን ይጠበቃል? በሚል ተተኳሪ ርዕስ ላይ በሚካሄደው ውይይት ላይ እንዲሳተፉና ገንቢ አስተያየትዎን እንዲሰጡ ተጋብዘዋል፡፡ የውይይቱን ውጤት መሠረት በማድረግ ተግባራዊ ሥራ በመሥራት የሀገራችን ሕጻናት በሙሉ 4ኛ ክፍል ሲደርሱ በአፍ መፍቻ፣ በ2ኛም ሆነ በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች አቀላጥፈው እንዲያነቡ ለማስቻል እያንዳንዳችን የዜግነት ግዴታችንን በመወጣት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የበኩላችንን አስተዋጽዖ የምናበረክትበት ጅማሮ ይሆናል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት