ተማሪ ጽጌሬዳ ግርማይ ከአባቷ ከአቶ ግርማይ ገ/መድኅን እና ከእናቷ ከወ/ሮ ያበሻ ያዘዘው ወልቃይት ወረዳ አዲ ረመጽ ከተማ በ1993 ዓ/ም ተወለደች፡፡

ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ የመሰናዶ ትምህርቷን በወልቃይት ጌታቸው አዘናው 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትላለች፡፡  ፎቶዎችን ለማየት

ከመስከረም 2012 ዓ/ም ጀምሮ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመመደብ በሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት የ2ኛ ዓመት ተማሪ የነበረችው ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ ጥር 23/2014 ዓ/ም ከቅርብ ጓደኛዋና አብሯት ከሚማረው ተማሪ በተሰነዘረባት ድንገተኛ ጥቃት በስለት ተወግታ በ20 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡ የሽኝት ሥነ-ሥርዓት በጫሞ ካምፓስ ጥር 24/2014 ዓ/ም ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ ተደርጎ አስከሬኗ ወደ ቤተሰቦቿ ተልኳል፡፡

የግድያ ወንጀሉ ተጠርጣሪ ተማሪ በሕግ ቁጥጥር ሥር ውሎ ፍ/ቤት የቀረበ ሲሆን ማስረጃዎች እስኪጣሩ በማረሚያ ቤት እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተማሪ ጽጌሬዳ ድንገተኛ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿ እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በሙሉ መጽናናትን ይመኛል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት