የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን ነባር ቅድመ-ምረቃና ድኅረ-ምረቃ ክረምት መርሃ-ግብር ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ሐምሌ 11 እና 12 ቀን 2014 ዓ/ም ሆኖ ትምህርት የሚጀመረው ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ/ም መሆኑን ያሳውቃል፡፡

በመሆኑም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ/ም ነባር ቅድመ-ምረቃና ድኅረ-ምረቃ ክረምት መርሃ-ግብር ተማሪዎች በሙሉ በተጠቀሱት ቀናት በየካምፓሶቻችሁ ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በአካል ቀርባችሁ ምዝገባ እንድታካሂዱ እየገለጽን ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ቱቶሪያል ሐምሌ 11 እስከ 16 ቀን 2014 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት