አርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ‹‹Ethio Jobs›› አጋር ድርጅት ከሆነው ‹‹Derja.com›› ጋር በመተባበር ለ2014 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች ‹‹Self Discovery››፣ ‹‹Building Self Image››፣ ‹‹Communication at the Work Place››፣ ‹‹Analytical Thinking››› በሚሉና ሌሎችም ርዕሶች ዙሪያ ከሰኔ 17-21/2014 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሙያ ማበልፀጊያ ማዕከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪ መምህርት ስለእናት ድሪባ እንደገለጹት ከ2014 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ የድርጅቱን የመመዘኛ መስፈርቶች ያሟሉ ተማሪዎችን በ‹‹Dereja Academy Acceleratory Program(DAAP)›› በማካተት በቀጣሪ ድርጅት አስፈላጊ ናቸው ተብለው የተመረጡ ሰዋዊ እና ፕሮፌሽናል ርዕሰ ጉዳዮችን በ8 ሞጁሎች በማዘጋጀት ሥልጠናው ተሰጥቷል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ሠልጣኞቹ ወደ ሥራ ዓለም ለመግባት ብቁና ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን አስፈላጊ ክሂሎት እንደሚመረቁበት የትምህርት ዘርፍ ድርጅቱ ዕውቅና በሰጣቸው መምህራን ሥልጠና የወሰዱ መሆኑን መ/ርት ስለእናት ተናግረዋል፡፡ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ለሚመረቁ ተማሪዎች ሥልጠናውን ለመስጠት የምዘና ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ሠልጣኞች በሰጡት አስተያየት ሥልጠናው ለሥራ ፈጠራ የሚረዱ ክሂሎቶችን፣ በግልም ሆነ በመደራጀት ችግሮችን መፍታትና ለትልቅ ዓላማ መብቃት የምንችልበትን እንዲሁም ተመርቀን ስንወጣ ከተቀጣሪነት ባለፈ ቀጣሪ የምንሆንበትን መንገድ ያሳየ ነው ብለዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት