አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ/ም የነባር የክረምት መርሃ-ግብር ትምህርት የምዝገባና የትምህርት መጀመሪያ ጊዜ አስመልክቶ በቴሌቪዥን፣ በዩኒቨርሲቲው ድረ ገጽና ማኅበራዊ ትስስር ገጾች ምዝገባ ሐምሌ 11-12/2014 ዓ/ም እንዲሁም ትምህርት የሚጀምርበት ጊዜ ሐምሌ 13/2014 ዓ/ም መሆኑን ማስተዋወቁ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ከትምህርት ሚኒስቴር በ27/10/2014 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ በኮቪድ - 19 እና በሰሜኑ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የአጠቃላይ ትምህርት ተማሪዎች መደበኛ የትምህርት መርሃ-ግብር በተቀመጠለት ጊዜ ባለመጠናቀቁ የ2014 ዓ/ም የክረምት የመምህራንና የት/ቤት አመራሮች ደረጃ ማሻሻያ ትምህርት ከሐምሌ 20/2014 ዓ/ም እስከ መስከረም 10/2015 እንዲካሄድ ስለተገለጸ በዚሁ አግባብ ማሻሻያ በማድረግ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምዝገባ ጊዜ ሐምሌ 20-21/2014 ዓ/ም እንዲሁም ትምህርት የሚጀመርበት ጊዜ ሐምሌ 22/2014 ዓ/ም መሆኑን በድጋሚ ያሳውቃል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ