መምህር በልስቲ ሌሊሳ ከአባታቸው ከአቶ ሌሊሳ ፊጣ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ሽታዬ አንዱዓለም የካቲት 25/1976 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ክፍለ ሀገር ፊንጨዓ ቀበሌ ተወለዱ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ፊንጨዓ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አምቦ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡

በ1994 ዓ/ም ከጅማ ዩኒቨርሲቲ አምቦ ኮሌጅ በኬሚስትሪ የትምህርት ዘርፍ በ‹‹Food & Sugar Technology›› በዲፕሎማ የተመረቁ ሲሆን ሐምሌ 2005 ዓ/ም ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በኬሚስትሪ ትምህርት የBSc ዲግሪያቸውን እንዲሁም በ2010 ዓ/ም በኢንደስትሪያል ኬሚስትሪ 2ኛ ዲግሪያቸውን አጠናቀዋል፡፡

ጥር 28/2002 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በቴክኒክ ረዳትነት ተቀጥረው ሥራ የጀመሩ ሲሆን በቴክኒክ ረዳትነት ከጥር 25/2003 - ጥር 23/2004 ዓ/ም በደረጃ 1፣ ከጥር 24/2004 - ጥር 23/2006 ዓ/ም በደረጃ 2፣ ከጥር 24/2006 - መስከረም 12/2008 ዓ/ም በደረጃ 3 እንዲሁም ከመስከረም 13/2008 - ጥር 25/2011 ዓ/ም በተቀዳሚ ረዳትነት ደረጃ 1 አገልግለዋል፡፡

መምህር በልስቲ ከየካቲት 2/2011 ዓ/ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው በሌክቸረር አካዳሚክ ማዕረግ በመምህርነት ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሐምሌ 15/2014 ዓ/ም በተወለዱ በ38 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመምህር በልስቲ ሌሊሳ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት