በአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የውሃ አቅርቦትና አካባቢ ምኅንድስና ት/ክፍልና በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ባዮሎጂ ት/ክፍል አስተባባሪነት ከሐምሌ 11-15/2014 ዓ/ም ለ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች የ ‹‹Python Programing Language›› ሶፍትዌር ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

የባዮሎጂ ት/ክፍል የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች አስተባባሪ ዶ/ር አሸናፊ ኃይሉ ሥልጠናው ለ‹‹Biotechnology››፣ ‹‹Infectious Disease›› እና ‹‹Biodiversity Conservation Management›› ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠና መረጃ ለመሰብሰብ፣ ለመተንተንና ኮድ ለማድረግ የሚረዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የውሃ አቅርቦትና አካባቢ ምኅንድስና ት/ክፍል መምህርና አሠልጣኝ ዳንኤል አሰሌ እንደተናገሩት ሥልጠናው ከዚህ ቀደም በ3 ዙሮች ለ100 የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራን የተሰጠ ሲሆን ተመራማሪዎችና የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች የምርምርና የመመረቂያ ጹሑፋቸውን በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ ለማሳተም የሚረዳ ነው፡፡ 

የ‹‹Infectious Disease›› የ3ኛ ዓመት ተማሪ አቶ መሐመድ ሰኢድ ከዚህ ቀደም መሰል ሥልጠና መውሰዳቸውን ተናግረው የሶፍትዌሩን አገልግሎት ተረድተንና በራሳችን ኮድ አድርገን መጠቀም መቻላችን የአሁን ሥልጠና ለየት ያደርገዋል ብለዋል፡፡

በሥልጠናው 13 የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት