በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት 13 ዓመታት የዘረመልና ዕፅዋት እርባታ መምህርና ተመራማሪ በመሆን ያገለገሉት ፕ/ር አብዱልቀይም ክሃን (Prof Abdul Qayyum Khan) በዘረመል፣ ዕፅዋት እርባታ፣ ዕፅዋት ፊዚዮሎጂ፣ የዘር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ ሴልና ሞለኪውላር ባዮሎጂ እና ባዮቴክኖሎጂ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተጻፉ 100 መጻሕፍትን ለዩኒቨርሲቲው ቤተ መጻሕፍት ለግሰዋል።ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ፕ/ር አብዱልቀይም የአገልግሎት ጊዜያቸውን አጠናቀው ወደ ትውልድ ሀገራቸው ሕንድ ከመመለሳቸው በፊት በመምህርነትና በምርምር ቆይታቸው እንዲሁም በተለያዩ ጊዜያት ከሀገራቸው ሲመለሱ ለዚህ ዓላማ አስበው የሰበሰቧቸውን መጻሕፍት ለዩኒቨርሲቲው በማበርከታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ፕ/ር አብዱልቀይም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በነበራቸው የሥራ ቆይታ በባዮቴክኖሎጂ፣ በሸንኮራ አገዳ ምርት ቴክኖሎጂ፣ በአግሮኖሚ እና በዕፅዋት እርባታ የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ መርሃ ግብር ኮርሶችን በማስተማር፣ በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ላይ የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን በማካሄድ፣ በተለያዩ የምርምር ፕሮጀክቶች ላይ ተባባሪ ተመራማሪ በመሆን እንዲሁም ለ2ኛ ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፎች አማካሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት