የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው በአካባቢው ያለውን የውሃ ተፈጥሮ ሃብትን ለትራንስፖርትና መሰል ተግባራት ለማዋል በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ጥቅምት 14/2015 ዓ/ም ውይይት አድርገዋል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

በውይይቱም መሠረት የተለያዩ ሥልጠናዎች እንደሚዘጋጁና ከሁለቱም ወገን የተወጣጡ ኮሚቴዎች እንደሚዋቀሩ እንዲሁም  አብሮ  ለመሥራት የጋራ ሥምምነት እንደሚፈጸም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

በውይይቱም የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር እና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው፣ የኢትዮጵያ ማሪታይም ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንትና ምክትል ፕሬዝደንቶች እንዲሁም የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ም/ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር  እና ሌሎችም የክብር እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡  

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት