በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮሎጂ ትምህርት ክፍል «Bio Diversity Conservation and Management» ትምህርት ፕሮግራም ላላፉት 5 ዓመታት የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት እጩ ዶ/ር ተመስገን ዲንጋሞ የምርምር ሥራቸውን ጥቅምት 21/2015 ዓ/ም የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎች በተገኙበት አቅርበው ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ


የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማግኘት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት በመምህርነት ሲያገለግሉ ቆይተው የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በ2010 ዓ/ም አጋማሽ ላይ የጀመሩት እጩ ዶ/ር ተመስገን የመመረቂያ ጽሑፋቸውን በ ‹‹Land Cover Changes, Vegetation Ecology, and Carbon Stock Estimation in the Western Escarpment of Rift Valley in the Gamo Zone, Southern Ethiopia›› በሚል ርዕስ ላይ አከናውነዋል፡፡


የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የባዮሎጂ ት/ክፍል መ/ርና የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ክትትልና ትግበራ ዳይሬክተር ዶ/ር ሠረቀብርሃን ተከተል እንደገለጹት በ3ኛ ዲግሪ በርካታ የተማረ ኃይልን ለማፍራት ዩኒቨርሲቲው በትኩረት እንደሚሠራና በ2022 ማጠናቀቂያ ላይ  50% ያህሉ መ/ራን የ3ኛ ዲግሪ እንዲኖራቸው እንደሚፈልግ ጠቁመዋል፡፡


እጩ ዶ/ር ተመስገን የዶክትሬት ዲግሪያቸው በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ከጸደቀ በኋላ የሚያገኙ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ክትትልና ትግበራ ዳይሬክተርን ጨምሮ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መ/ር ፕሮፌሰር ዘርይሁን፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የዘርፉ መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡


                                                                                                                                                                                                                                      የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት