የአፍሪካ ወጣቶች ወር በአፍሪካ ደረጃ “Breaking the Barriers to Meaningful Youth Participation and Inclusion in Advocacy” በሚል መሪ ቃል ከኖቨምበር 01/2022 እ.ኤ.አ ጀምሮ እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን በሀገራችን ደግሞ በነገው ዕለት ከጧቱ 02፡30 ጀምሮ በዋናው ግቢ በሚገኘው ትልቁ አዳራሽ “ንቁ የወጣቶች ተሳትፎና ተካታችነት ለስብዕና ልማት” በሚል መሪ ቃል ለ16 ጊዜ  ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የወጣቱን ግንዛቤ፣ ተሳትፎና ስብዕና በሚገነባ መልኩ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች የሚከበር ይሆናል፡፡  በልዩ ትኩረት በትምህርትና ስብዕና ልማት፣ ወጣትና ሥራ ፈጣሪነት፣ የወጣቶች ተዋልዶ ጤናና ስብዕና ልማት እና አደንዛዥ ዕጽ በወጣቶች ስብዕና ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖና ሌሎችም የውይይት ጉዳዮች የተካተቱበት ይሆናል፡፡

ስለሆነም የተወደዳችሁ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንኳን ወደ ዩኒቨርሲቲያችን ደህና መጣችሁ እያልን በነገው ዕለት የፌዴራል፣ የዞን፣ የከተማውና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በኢትዮጵያ ደረጃ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሚከበረው የአፍሪካ ወጣቶች ወር አከባበር ላይ እንድትታደሙ የተጋበዛችሁ መሆኑን እየገለጽን በዚሁ አጋጣሚ ለበዓሉ ድምቀት ሲባል የሬጂስትራር የምዝገባ አገልግሎት በጧት የማይሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት